የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች 23ኛውን ዓለም...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- In News    0

የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች 23ኛውን ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በማስመልከት የፓናል ውይይትአካሄደ

የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች 23ኛውን ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በማስመልከት የፓናል ውይይትአካሄደ
አዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች፤ ህዳር 10 ቀን 2019 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት 23ኛውን ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን “ሥውር ትስስሮችን በማጋለጥ፤ የሙስና ወለድ ወንጀሎችን ሰንሰለት እንበጥስ” በሚል መሪ ቃል በማስመልከት የግንዛቤ መድረክ አካሂዷል።
ህዳር 10 ቀን 2019 ዓ.ም በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በተካሄደው በዚህ መድረክ የፍርድ ቤቱ ምክትል ፕሬዚዳንት፣ የፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፣ የየምድብ ችሎቱ አስተባባሪ ዳኞች፣ ዳኞችና የፍርድ ቤቱ ሠራተኞች ተሳትፈዋል።
መድረኩን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት የፍርድ ቤቱ ምክትል ፕሬዚዳንት ክብርት ወ/ሮ ፍራኦል ቶሎሳ  ሲሆኑ  የዘንድሮው የፀረ-ሙስና ቀን መሪ ቃልና የበዓሉ አከባበር ዓላማ ላይ ማብራሪያ ሰጥተው በመድረኩ የሚቀርበው ሰነድ የሙስናን ዓለም አቀፋዊ ሁኔታ፣ የሙስና ወንጀል ዓይነቶች፣ በመንግሥት ተቋማት የተወሰዱ የመከላከል እርምጃዎችና የወደፊት ቅድሚያ አቅጣጫዎችን እንደሚዳስስ ገልጸዋል።
በመቀጠልም የፍርድ ቤቱ የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እሸቱ ሃይሌ የዝግጅቱን ዋና ሰነድ አቅርበዋል። ሰነዱ የሙስናን ምንነትና ተፅዕኖ፣ የሙስና ወንጀሎችን፣ ሥውር ትስስሮችን የማጋለጥ አስፈላጊነት፣ የመከላከያ ስልቶችን እንዲሁም በከተማ ደረጃ የተከናወኑ ሥራዎችን፣ ያጋጠሙ ፈተናዎችንና ቀጣይ አቅጣጫዎችን የያዘ ነበር።
ሰነዱ ቀረበ በኋላ በፍርድ ቤቱ ምክትል ፕሬዚዳንትና በፕሬዚዳንቱ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ መሪነት በሰነዱ ይዘት ላይ ውይይት ተካሂዷል። በውይይቱም የቀረበውን ሰነድ እንደ መነሻ በመውሰድ በፍርድ ቤቱ የሥራ አካባቢ ተግባራዊ ማድረግ፣ ሁሉም የተቋሙ ሠራተኞች ሙስናን በመከላከል ረገድ የየራሳቸውን ኃላፊነት እንዲወጡና ከሙስና የፀዳ የሕዝብ አገልጋይ ለመሆን ቁርጠኛ እንዲሆኑ የሚያስችሉ ሃሳቦች ተነስተዋል።
በተያዘም በዚሁ መድረክ የፍርድ ቤቱን የዲጂታል ሀብት ምዝገባ ማስጀመር ስራ እንደሚከናወን ተገልፆ በተሰጠው ማብራሪያ መሠረትም የሀብት ምዝገባው ከህዳር 15 ጀምሮ በተቋሙ ከፍተኛ ኃላፊዎችና ዳይሬክተሮች በመጀመር እንደሚሰራና ይህም የሀብት ግልጽነትንና ተጠያቂነትን ለማጠናከር የሚያግዝ እርምጃ መሆኑ ተጠቁሟል።
በመድረኩ መደምደሚያ ላይም የፀረ-ሙስና ቀንን በማስታወስ ብቻ ሳይወሰን ፍርድ ቤቱን ከሙስና የፀዳ፣ በግልጽነትና በተጠያቂነት መርሆዎች የሚመራ እንዲሁም በቴክኖሎጂ የታገዘ ተቋም ለማድረግ የሁሉም አመራርና ሠራተኛ ተሳትፎ አስፈላጊ መሆኑ ተገልጿል።
በአጠቃላይ መድረኩ የፀረ-ሙስና ትግል የአንድ ክፍል ወይም የአንድ ኃላፊ ብቻ ኃላፊነት ሳይሆን የተቋሙ ሁሉም አባላት የጋራ ተልዕኮ መሆኑን በማጉላት፣ ግልጽ፣ ተጠያቂና ከሙስና የፀዳ የፍትሕ ተቋም ለመገንባት ያለውን ቁርጠኝነት ያሳየ ሆኗል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments