The 22nd International Anti-Co...

image description
- In News    0

The 22nd International Anti-Corruption Day was celebrated with a panel discussion under the theme: Ethics for a Generation; Institutions for Action

የአዲስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ተስፋዬ መለሰ እና ም/ፕሬዝደንት ክብርት ወ/ሮ ፍራኦል ቶለሳ በመድረኩ ተገኝቶ  ስለ አላማ እና አስፈላጊነት የመግብያ ንግግር አድረገዋል፡፡መድረኩም በሁለት ዙር የተከበረ ሲሆን  አለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን ምክንያት በማድረግ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በትዉልድ ግንባታ ያለዉን ሚና በብቃት እንዲወጣና ተቋማትም ለብልሹ አሰራር የሚያጋልጣቸዉን የአሰራር ክፍተት በጥናት እየለዩ በመዝጋት ፍትሀዊና ቀልጣፋ አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት እንዲኖራቸዉ ማስቻል እጅግ አስፈላጊ ነዉ ብለዋል፡፡ ሥነ-ምግባር ያለው ትውልድ፤ከሙስና የፀዳ የአሰራር ስርዓት ያለው ተቋም መገንባት የሁላችንም ሃላፊነት መሆን እንዳለበት በአፅኖት አንስተዋል፡፡
ሥነ-ምግባር እሴቶች ላይ የተመሰረት ትውልድ እና ከሙስና የፀዳ ስርዓት ጋር ራሳቸውን አላምደው  ተቋማችን የዘላቂ ልማት፣የማህበራዊ እምነት እና የመልካም አስተዳደር መሰረት እንደሚሆን ተጠቁመዋል፡፡ በስነ ምግባር የታነፁ ዜጎች በታማኝነት፣በተጠያቂነትና በፍትሃዊነት የሚሰሩ ሲሆን የሙስና ተጋላጭነታችንን በአሰራር በመዝጋት ተቋማችንን የዳኝነት አገልግሎት ደግሞ ቅልጥፍናን፣ፍትሃዊነትን የህዝብ አመኔታን ያረጋግጣሉ ብለዋል፡፡ስለሆነም በድረኩም በስነዱ ላይ ሙስና ለግል ጥቅም ወይም ለቡድን ጥቅም ሲባል ስርአት ፣ህግ፣ ደንብ አሰራር እንዲሁም መርሆዎችን የጣሰ ማንኛውም ተግባር መሆኑ የስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ እሸቱ ሀይሌ ተገልጿል።በተለያዩ ኩነቶች በጥያቄ እና መልስ፤የግጥም ሥንኞች በማዘጋጀት በድምቀት ተከብረዋል፡፡ በምክክር ወቅት ተገልጋይ እምነት ማጣት  ዬለበትም የግንዛቤ ስራ መሰራት አለበት፤የጋራ እሴታችንን በጋራ መገንባት ግዴታችን ነዉ በማለት ተሳታፊዉ አንስተዋል፡፡ በመጨረሻም በበጀት አመቱ በሥነ ምግባራቸዉ አርዓያ እና ምሳሌነት፤ ሙስናን በመከላከል ረገድ ከፍተኛ ሚና ለነበራቸዉ ዳኞች እና ባለሞያዎች የእዉቅና ምስጋና ሰርተፊኬት በማበርከት መድረኩ ተጠናቀዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments