የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤት የ2013 የ6 ወራት ስራ አፈፃፀም ሪፓርት ለከተማው ምክር ቤት አቅርቧል።

ምክር ቤቱም የፍርድ ቤቱን የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም በማድነቅ የፍርድ ቤቱ ችግሮች እንዲፈቱ ትብብር እንደሚያደርግ ቃል ገብቷል። በተጨማሪም ፍርድ ቤቱ የ5 የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት እና የ16 የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች ሹመት ለምክር ቤት አቅርቦ አፀድቋል።